ከ11 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች $640,000 ዶላር በሊባኖስ ከሚገኙ የቤት ሠራተኞች በመዝረፍ አሜሪካ ለሚገኝ የህግ ተቋም እንዲተላለፍ አደረጉ

ነሐሴ 10 2012 ዓም

ዘካሪያስ ዘላለም፤ ለአዲስ ስታንዳርድ

በስተግራ አምባሳደር ተክለአብ ከበደ፥ እንዲሁም በስተቀኝ አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ። ለአዲስ ስታንዳርድ የደረሱት ሰነዶች ክምር እንደሚያሳዩት ሁለቱም አምባሳደሮች በቀጥታ በዚህ አወዛጋቢ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ የዛሬ 11 ዓመት እጃቸው እንደነበረበት ነው። አምባሳደር ተክለዓብ ከዲፕሎማሲ አገልግሎት በጡረታ የተገለሉ ሲሆን፥ በአዲስ አበባ የንግድ ሥራ ላይ ናቸው፣ አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሰራሉ።

ይህ ሪፖርት ከሁለቱም አምባሳደሮች ጋር የተደረጉ ቃለምልልሶችን የያዘ ነው፤

በ2019 እ.ኤ.አ. መገባደጃ ላይ ለአዲስ ስታንዳርድ ከደረሰ የጥቆማ ሰነድ በመነሳት ተከትሎ ባደረግናቸው ምርመራዎች በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ንብረት የሆነ ገንዘብ በኢትዮጵያ መንግስት ተመዝብሮ በምስጢር ለአሜሪካ የሎቢ ድርጅት የዕዳ ክፍያ እንዲሆን $600,000 የሆነ መጠን ያለው ክፍያ መፈጸሙ ተደርሶበታል።

በጅዳ፥ሳውዲ አረቢያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በኩል በሚያዝያ 2009 እ.ኤ.አ. የአጠራጣሪ የሆነ የገንዘብ ማስተላለፊያ የተደረገ ሲሆን፥ ይህም ገንዘብ ዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የተባለ በ2000ዎቹ ውስጥ ለኢትዮጵያ መንግስት የህዝብ ግንኙነት እና ሎቢዪንግ ሥራዎች በመፈጸም ለሚታወቅ እና በዋሽንግተን መቀመጫውን ያደረገ ሕጋዊ አካል ንብረት ወደሆነ የባንክ ሒሳብ መዝገብ ገቢ ተደርጓል። ዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የሚለው ስም ቀድሞ በ2007 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ማህደር የሚወቅሰው መግለጫ እንዲታፈን ለማድረግ የአሜሪካ የሕግ አውጭዎችን በተሳካ ሁኔታ በማሳመኑ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚታወቅ የወል ስም ሆኖ ነበር።

ዳሩ ግን፥ ለወራት የተደረጉ ምርመራዎችን ተከትሎ አዲስ ስታንዳርድ አሳማኝነታቸውን ካረጋገጣቸው የጥቆማ ሰነዶች በመነሳት፥ ለዲ/ኤልኤ ፓይፐር ክፍያ ለመፈጸም በኢትዮጵያ ሹሞች ጥቅም ላይ የዋለው ጠቅላላ ገንዘብ የኢትዮጵያ መንግስት ንብረት ብቻ እንዳልሆነ ተደርሶበታል። ደግሞም በርካታ የመንግስት ተወካዮች፥ ቢያንስ በሁለት አገራት የሚገኙ አምባሳደሮችን ጨምሮ፥ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ይህንን በደንብ ያውቅ እንደነበረ ተጋልጧል።

ከተገኙት ሰነዶች መካከል የገንዘብ ዝውውር መደረጉን የሚያስረዱ እና በ2015 እ.ኤ.አ. በጅዳ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ከተደረገው ኦዲት ሰነዶች አንድ አካል ተደርገው የተያዙ ደብዳቤ እና ደረሰኞች ይገኙበታል።። ለዲ/ኤልኤ ፓይፐር የተፈጸመው የ$600,000 ክፍያ የተመዘገበረው ከማህበረሰቡ ልገሳ ላይ ሲሆን ይህም፥ በሳውዲ አረብያ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቆንስል በነበሩት ተክለአብ ከበደ አረጋዊ፥ እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገንዘብ መምሪያ ስታፍ አባል እና በፈረንሳይ አምባሳደር የነበሩት ነጋ ጸጋዬ ቁጥጥር ሥር የተከናወነ ነው።

1Amb Nega

ይህ ደብዳቤ በኤምኤንድ ባንክ ቅርንጫፍ ለሚገኘው የዲ/ኤልኤ ፓይፐር ሒሳብ የተያዙ መረጃዎችን ያካተተ ነው።፤ ፊርማ ያኖሩበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገንዘብ መምሪያ ሹም፥ ነጋ ጸጋዬ፣ ናቸው። እርሳቸው ቀጥለው በፈረንሳይ እና በስፔን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወደመሆን ተሸጋግረዋል። በሥራ ልምዳቸው ዲፕሎማት የሆኑት አምባሳደር ነጋ፥ አሁን ተመልሰው በአዲስ አበባ የሚገኙ ሲሆን፥ ለውጭ ጉዳይ የህዝብ ዲፕሎማሲ ማስታወቂያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመስራት ላይ ናቸው።

ገንዘቡ ሙሉ በሙሉ በሊባኖስ እየማቀቁ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአገር ውስጥ ሠራተኞችን ጥቅም ለማስጠበቅ የታለመ ነበረ። ይህም ድምር የማህበረሰብ ዝግጅቶን በማድረግ የተሰባሰበ እና ከማህበረሰቡ አባላት እና የኃይማኖት ተቋማት የግል ልገሳ ተደርጎ በአስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የተጠራቀመ ነበረ። አያሌ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ወታደራዊ ግጭት የተነሣ በ2006 እ.ኤ.አ. ወጥተው ሲሔዱ፥ ይህ ገንዘብ ከቤይሩት ወደጅዳ ተላልፎ፥ ለአምባሳደር ተክለአብ ከበደ በዐደራ ተሰጥቶ ሊባኖስ እስክትረጋጋ እና ማህበረሰቡም ዳግም እስከሚገነባ ድረስ እንዲጠበቅ ሆነ።

ዳሩ ግን፥ ገንዘቡ ፍጹም አልተመለሰም፤ መሠረቱን በሳውዲ ያደረገው የኢትዮጵያ ቆንስላ ስለዚህ ነገር ድጋሚ አላነሳም፥ ደግሞም በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ላቀረበለት ጥያቄም ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ቀረ። በሊባኖስ ያሉት ኢትዮጵያውያን ገንዘቡ ወደጅዳ ስለመተላለፉ ያውቁ የነበረ ቢሆንም፥ ከዚያ በኋላ ስለተፈጠረው ነገር ለእነርሱ እንዲያውቁ አልተደረገም ወይም ምክር አልተጠየቁም። ከስደተኛ ሠራተኞች ጋር በተገናኘ ድጋፍ ለማድረግ የወጣው ዕቅድ የውሃ ሽታ ሆነ።

በሊባኖስ የሚገኙ ስደተኛ ሠራተኞች በአገሪቱ የአሠሪ እና ሠራተኛ ሕግ ጥበቃ የላቸውም። በተቋማዊው ‹‹ከፋላ›› ሥርዓት መሠረት፥ የኢትዮጵያ ዜጋ የሆኑ ሠራተኞች የሚከፈላቸው ዝቅተኛ ነው፥ አልፈ አልፎም አሠሪዎቻቸው ይጎሳቆላሉ በደል ያደርሱባቸዋል ህይወታቸውም ያልፋል። ጨቋኝ አሰሪዎቻቸውን ለማምለጥ ሰማይጠቀስ ከሆኑ ህንጻዎች በረንዳዎች ራሳቸውን እየፈጠፈጡ ሆስፒታል የሚገቡ ሴት ኢትዮጵያውያን ቁጥር እያሻቀበ ሲመጣ፥ የማህበረሰቡ መሪዎች ሕዝቡን በማስተባበር ለህክምና ወጪዎች ሽፋን እንዲሆን አስበው የሒሳብ መዝገብ ከፈቱ። ይህም ገንዘብ የሟች ቤት ሰራተኞችን አስክሬን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በማድረስ ሥርዓተ ቀብራቸው እንዲፈጸም ማድረግን የመሣሠሉትን ወጪዎችንም እንዲሸፍን የታሰበ ነበር።

በሊባኖስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እና የኢትዮጵያ ቆንስል የሚያንቀሳቅሰው የነበረው ገንዘብ በጅዳ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ እንዲተላለፍ መደረግ የጀመረው በ2005 እ.ኤ.አ. አንስቶ ነው። ይህ ማህበረሰብ በጅዳ ወደሚገኘው የቆንስላ ንብረት ወደሆነ የባንክ ሒሳብ ሐብቶቹ መዛወር ከመጀመሩ አስቀድሞ ስለተደረገው ውሳኔ እንዲያውቅ ተደርጎ ነበረ። በወቅቱ በጅዳ ጠቅላይ ቆንስል የነበሩት አምባሳደር ተክለአብ፥ የሊባኖስ የፖለቲካ ቀውስ እና እስራኤል ሊባኖስን በቦምብ የማጋየት ዘመቻዋ ሲጠናቀቅ ሁሉንም ሐብቶች ሊመልሱ ይገባ ነበር። የኢትዮጵያ ቆንስል ንብረት ከነበረው መጠን ላይ ምን ያህሉ እንደተላለፈ ባይታወቅም፥ ከማህበረሰቡ የአገር ውስጥ ሠራተኞች ፈንድ የወጣው ገንዘብ መጠን በድምሩ $640,000 ነበር።

ዳሩ ግን፥ ማህበረሰቡ ገንዘቡን በፍጹም አላስመለሰም። ምንም እንኳን በቤይሩት የሚገኘው ቆንስላ አዲስ ሰራተኞች ቢቀጥርም እና ወደ ሊባኖስ የሚመለሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ቢያይልም፥ የጅዳው ቆንስላ ገንዘቡን አልመለሰም፣ ደግሞም በእጁ እንደነበረም በይፋ እውቅና አልሰጠበትም። ጥቃት የደረሰባቸውን ሠራተኞች ለመርዳት ቀድሞ የተጀመረውን ጥረት ለመገንባት ገንዘቡን መጠቀም ፈልገው የቀረቡ የማህበረሰቡ አባላት፥ ንብረታቸው ወደሳውዲ አረቢያ ከተዛወረ በኋላ ስለደረሰበት ሁኔታ ምላሽ ያገኙ ዘንድ የኢትዮጵያን መንግስት ሲጎጉቱ ነበረ። አንድ የማህበረሰቡ መሪ እንደውም በአዲስ አበባ ወደሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ቀርበው መልስ እስከመጠየቅ ደርሰው ነበረ። እርሳቸው ያደረጉት ጥረት ፍሬ አልባ ከመሆኑ ሌላ በሸፍጡ እጃቸውን ያስገቡ ዲፕሎማቶች ድምጻቸውን አጠፉ። ይህ በደፈናው ዝምታን መምረጣቸው ከዚያ በማስከተል በዩናይትድ ስቴትስ ወደሚገኘው ዲ/ኤልኤ ፓይፐር ገንዘቡ ሲዛወር ዱካው እንዳይታውቅ ዕድልን ፈጠረ። ለአዲስ ስታንዳርድ በምስጢር የተላለፉ ሰነዶች ባለፉት አስርት ዓመታት ገንዘቡ ምን እንደሆነ ሲያብሰለስሉ ለነበሩ ምላሽን ያስገኘ ነው።

ከግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሆነ ከልገሳ የተገኘ ገንዘብ ያሸሹት እነማን እንደነበሩ ከማጋለጥ በተጨማሪ፥ አዲስ ስታንዳርድ፥ በግላቸው ምርመራ በማድረግ ከዲ/ኤልኤ ፓይፐር ጋር ውል ስለመደረጉ ያወቁ ግን የማይመለከታቸው የነበሩ በርካታ ሌሎች የመንግስት ሹማምንትንም ለይቷል። እነዚህ ሹማምንት ማንም ሰው በ2009 እ.ኤ.አ. ለተደረገው ምዝበራ እንዳይጠየቅ፥ ዝምታቸውን በማዋጣ እና ለሕዝብም ከማጋለጥ በመቆጠብ የራሳቸውን ሚና ተጫውተዋል።

ከእነዚህም መካከል፥ የቀድሞ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ዋና ቆንስል፥ አምባሳደር ሐሊማ መሐመድ ናቸው። አምባሳደር ሐሊማ በሊባኖስ የሚገኘው ማህበረሰብ ህብረት በ2009 እ.ኤ.አ. ሊባኖስ ውስጥ በቤት ሥራ በሣምንት ሰባት ቀን እየለፉ በወር 100$ ብቻ የሆነ ገቢ ካላቸው ሴቶች የተመሠረተ መሆኑን በደንብ ያውቃሉ።።

አምባሳደር ሐሊማ መሐመድ፣ በቤይሩት የቀድሞ ዋና ቆንስል (ምስል፡ በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ)

ያላቸው ገቢ አነስተኛ ሆኖ ሣለ፥ ኢትዮጵያውያኑ ተረባርበው ችግር ላለባቸው ወገኖቻቸው ድጋፍ ለማድረግ ሞከረዋል የሚሉት የአባታቸውን ስም ያልሰጡን ሕይወት የተባሉት ናቸው። ሕይወት በሊባኖስ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ኖረዋል፣ ደግሞም ለዚህ ፈንድ ልገሳ ካደረጉት መካከል ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት፥ እንደዚህ ዓይነት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲጠፋ መደረጉ፥ በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት ላይ ‹‹የሞራል ውድቀት የሚያስከትል ቡጢ ነበረ።››

‹‹የሚያሳዝን ነው፥ ያን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ ለማሰባሰብ በጣም ረዥም ጊዜ ወስዶብናል። በጅዳ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሹማምንቶች እርግጠኛ ነኝ ስለዚህ ነገር ያውቃሉ። ይህንን ያህል ገንዘብ ሊጠፋ የሚችልበት ምንም መንገድ የለም። ዳሩ ግን ለእኛ ምንም ዓይነት ነገር አልተነገረንም።

በማህበረሰቦቹ ክበብ በተደጋጋሚ የሚነሣው የውይይት ርዕስ የዛሬ አስር ዓመት የነበረው ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ23 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ የሆነው ገንዘብ ወዴት እንደገባ ነው። እነዚህ እንግዲህ ለአስርት ዓመታት በሊባኖስ የኖሩ እና አንዳንዶቹም ገንዘቡ መሰብሰቡን ተከትሎ ለህዝቡ ጥቅም ተሰብስበው የነበሩ በርካታ ፕሮጀክቶችን መለስ ብለው በቁጭት የሚያስታውሱ ናቸው። በሊባኖስ ያሉ የአገራችን ዜጎች የሆኑት የቤት ሠራተኞች ንብረት የሆነው 640,000$ ዶላር በእርግጥ የት እንደደረሰ ዕውነታው አሁን ድረስ በጥብቅ የተዘጋ ምስጢር ሆኗል። እስከአሁን ድረስ፤

ገንዘቡ ሳውዲ አረቢያ የገባበት ሁኔታ  

በጅዳ፣ ሳውዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ

ሊባኖስ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ራፊክ ሃሪሪ በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ቤይሩት ውስጥ ተገድለው ሲገደሉ ወደ 22 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን በማጣታቸው በየካቲት 2005 እ.ኤ.አ. ነውጥ ገጥሟት ነበር። በዚህ ጥቃት የተቆጡ ሊባኖሳውያን የኃሪሪ ምትክ የሆኑት፥ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኦማሪ ካራሚ ከስልጣን እንዲነሱ ጠይቀው በኋላም ስልጣናቸውን ያስለቀቀ ተቃውሞ አስከትሏል። ተቃዋሚዎች ሲያነሷቸው የነበሩት ጥያቄዎች የጎረቤታቸው ሦርያ ሠራዊት ለሦስት አስርት ዓመታት በአገሪቱ መቀመጡ እንዲያበቃ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ተግባራዊ እንዲደረግ በማድረግ ዙሪያ ያጠነጠኑ ነበሩ። በሚሊዮኖች የተመሩ ሠልፎች አገሪቱን ከኮቪድ 19 መቀስቀስ አስቀድሞ በ2019-20 እ.ኤ.አ. የሊባኖስ ተቃዋሚዎች እንዳደረጉት በአገሪቱ እንቅስቃሴዎች እንዲገቱ አድርጓል። ዳሩ ግን፥ በ2005 እ.ኤ.አ. ላይ የጎራ እና ፖለቲካ ግጭት ማዕበል ተዳመረበት።። የቦምብ ጥቃት እና ዒላማ ያደረጉ ነፍስ ግድያዎች በርካታዎች፥ ስደተኛ ሠራተኞችን ጨምሮ፥ በወጡበት እንዲቀሩ እና እንዲቆስሉ አድርጓል።

ከሐሪረ መገደል ተከትሎ ባለው ጊዜ ነው በነውጡ መሐል በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መጀመሪያ አገሪቱን ለቅቀው መውጣት የጀመሩት። ዳሩ ግን፥ ከዓመት በኋላ፥ የሊባኖስ ችግሮች ተባባሱ። ከእስራኤል እና ትጥቅ ያነገቡት የሔዝቦላ አማጺያን መካከል ያለው ውጥረት የገነፈለው ኋለኛው በእስራኤል ድንበር ውስጥ ሸምቆ ስምንት የእስራኤል ወታደሮችን መግደሉን ተከትሎ ነው። ለዚህ አጸፋ እንዲሆን እስራኤል አየር ኃይሏን ተጠቅማ ቦምብ በማስወንጨፍ በሊባኖስ የሚገኙ የሒዝቦላ ዒላማዎችን እንደምትመታ አወጀች። በ2006 እ.ኤ.አ. ከሰኔ እስከ ነሐሴ ድረስ፥ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በአገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የትየለሌ ህንጻዎችን ዶግ አመድ አድርገው፥በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹህ ሰዎች ገደሉ። በአየር የተደረገው ዘመቻ የፈጠረውን ውድመት ተከትሎ አገሪቱን ጥለው ለመሰደድ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ብዛት በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ሆነ።

በዚያን ጊዜ በቤይሩት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የነበሩት ዋና ቆንስል አደም ኑርሑሴን አደም ነበሩ። ከ2004 እ.ኤ.አ. አንስቶ በሊባኖስ እንደመቆየታቸው፥ እስራኤል ከምትፈጽመው የቦምብ ጥቃት ወረራ ለማምለጥ በናፈቁ ኢትዮጵያውያን ተወላጅ ሠራተኞች የማይቋረጥ ጥያቄ የተነሣ የተቆጡ፣ ጫና የበዛባቸው እና ችግር የተጋረጠባቸው መሆናቸው በሚድያ ዘገባዎች ሲገለጽ ነበረ። እርሳቸው ያኔ በ2006 እ.ኤ.አ. ባልቲሞር ሰን ለተባለው ሚዲያ ሲናገሩ ‹‹አብዛኛዎቹ አልተማሩም›› ብለዋል።። ‹‹አንዳንዶቹ ፓስፖርት ምን እንድሆነም አያውቅም፣ አብዛኛዎቹ ደግሞ ከስፖንሰሮቻቸው ያመለጡ በመሆናቸው ሕገወጥ ናቸው።››

ሕይወት ይህንን ጊዜ ‹‹ልክ እንደትላንት ትዝ ይለኛል›› ይላሉ።

‹‹የታደሉቱ አገሪቱን በጊዜ ለቅቀው ወጡ። ኤስራኤላውያን አውሮፕላን ማረፊያውን እንዲሁም በቤይሩት ያሉ መንገዶችን ሳይቀር በቦምብ መትተዋል።። እንግዲህ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአውቶብስ ታጭቀው፥ በጊዜው ደህንነቱ የማያሰጋ ወደሆነችው መዳረሻ፥ ወደሶሪያ ይሔዱ ነበረ።››

በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት (ምስል፡ ከጎግል ማፕ)

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይ/ኦ/ኤም) ቆይቶ በሊባኖስ ይንገላቱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን እንዲመለሱ እገዛ አደረገ። ከ2005 እ.ኤ.አ. ጀምሮ እና በ2006 እ.ኤ.አ. በቀጠለው የእስራኤል የአየር የቦምብ ጥቃት፥ ዋና ቆንስል አደም ኑርሁሴን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ይዞታ የሆኑ በርካታ ንብረቶችን በአስቸኳይ በጅዳ ወደሚገኘው ባንክ እንዲዛወሩ አዘዙ።

በሊባኖስ፥ በስደተኞች የሚመሰረቱ ማህበራት በሕጋዊ መንገድ መመዝገብ አይፈቀድላቸውም።። በሊባኖስ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚንቀሳቀስ በይፋ የሚታወቅ ምንም ዓይነት ድርጅት የለም፥ በቤይሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ በስተቀር። ይህም በሊባኖስ ለሚገኘው በስደተኞች ለሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ነገሮችን አወሳስቦበታል።። በራሱ ስም የባንክ ሒሳብ መዝገብ መክፈት ባለመቻሉ፥ ማህበረሰቡ ከቆንስላው ጋር ስምምነት አድርጎ የሰበሰበውን ገንዘብ በተለየ የባንክ ሒሳብ በቆንስላው ስም እንዲቀመጥ አድርጓል።

ማህበረሰቡ እና ቆንስላው በተስማሙት መሠረት ይህ ገንዘብ በማንኛውም ጊዜ ላይ ለማህበረሰቡ አመራሮች ክፍት የሚደረግ እና ከማህበረሰቡ በግልጽ ፍቃድ ሳይሰጥ የማይንቀሳቀስ ነበረ። መሠረት ወርቅነህ ከተሾሙ አቃቤ ነዋዮች መካል ነበሩ። እርሳቸውን አዲስ ስታንዳርድ አግኝቶ ሲያነጋግራቸው ወደአዲስ አበባ ተመልሰው ነበረ።

‹‹ወቅቱ የተዋከበ ነበር›› በማለት ይጀምራሉ።። ‹‹ማህበረሰባችን ተበታትኖ ነበር፥ ሰዎች ከሊባኖስ ለማምለጥ የሚችሉትን ሁሉ ሲያደርጉ ነበረ።››

መሠረት እንደነገሩን፥ ዋና ቆንስል የሆኑት አደም ኑርሑሴን የቀሩትን የቆንስሉን ስታፍ አባላት እና የማህበረሰቡን መሪዎች ለአስቸኳይ ስብሰባ የጠሩት በቦምብ ጥቃት ዘመቻው ወቅት ነበረ።

‹‹በቤሩት የሚገኘው የቆንስላ ጽህፈተ ቤት ደህንነቱ ስጋት ላይ እንደወደቀ ለእኛ አብራርተውልናል›› በማለት የምታስታውሰው መሠረት ‹‹አንድ ቀን መልሰን ማህበረሰባችንን መገንባታችን አይቀርም። ያ ጊዜ እስከሚመጣ ድረስ ግን፥ በእኛ ባንክ ሒሳብ የሚገኘው ገንዘብ በሳውዲ አረብያ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ይዛወራል››።

መሠረት ለአዲስ ስታንዳርድ እንደነገሩት ከሆነ፥ ዋና ቆንስሉ ሠላም ሲሆን ተወካዮች ዳግም እንደሚዋቀሩ እና ገንዘቡ በጅዳ ከሚገኘው ቆንስላ እንዲመለስላቸው ማህበረሰቡ ሊጠየቅ እንደሚችሉ ቃል ገብተዋል። ‹‹ጥርጣሬዎች አሉኝ፥ ዳሩ ግን ምን ምርጫ ይኖረናል? ያለነው በጦር ቀጠና ውስጥ ነው ደግሞም ይህ ገንዘብ እዚያው ሊታቀብ እና በሊባኖስ ባንኮች ዳግም እንዳይወሰድ ሊደረግ እንደሚችልም እንፈራለን።››

እንደመሰረት አባባል፥ በርካታ የቆንስላው ስታፍ አባላት ካላቸው የሥራ መደብ የከዱ ሲሆን፥ ዲፕሎማቶችም ይህንን ሊያደርጉ እንደሚችሉ አሳማኝ ስጋቶች ነበሩ።

ዋና ቆንስል አደም ኑርሁሴን በ2008 እ.ኤ.አ. የሆነ ጊዜ፥ ከመንግስት ከድተው ላይ ከሊባኖስ መሸሻቸው እና በአሜሪካ አዲስ ህይወት መጀመራቸው አልቀረም። ከዚህ ክህደት አስቀድሞ፥ ከተለያዩ የሚዲያ ምንጮች ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ተስፋ እንደቆረጡ ይታይባቸው ነበር።። በኢትዮጵያውያን ላይ በሚደርሰው የበደል፣ እስራት እና ህልፈተ ህይወት ጉዳዮች በመጥለቅለቃቸው፥ በ2007-08 እ.ኤ.አ. መካከል ኢትዮጵያውያን ዜጎች ራሳቸውን ያጠፉባቸው 148 አከባቢ ጉዳዮች በጽህፈት ቤታቸው እንደሚገኝ ለሊባኖስ ጋዜጠኛ ተናግረው ነበረ። ‹‹በእያንዳንዱ ቀን እስከ አምስት የሚደርስ የበደል ጉዳዮች ይደርሱናል›› በማለት ዋና ቆንስሉ ተናግረዋል። ደግሞም ‹‹ዘመናዊ ባርያ አሳዳሪነት›› ብለው የሚጠቅሱትን ለማስቆም የሊባኖስ ባለስልጣናት የበለጠ ምንም ላለማድረጋቸው በተጠያቂነት ይወነጅሏቸው ነበረ። ለስፔይን የሚዲያ ምንጭ ለሆነው ኤል ሙንዶ በሰጡት አስተያየት፥ ‹‹ቅሬታዎቻችን ከላይ ላሉት ሹሞቻቸው እንኳን አይደርስም›› ሲሉ ተቆጥተዋል። የሥራ ቅጥር ወኪሎችንም ‹‹ባርያ ነጋዴዎች›› በመሆን እያገለገሉ ነው በማለት ወንጅለዋል።

 

ከጅዳ ወደ አሜሪካ

በ2010 እ.ኤ.አ. በሊባኖስ ከፍተኛ ዲፕሎማት እንዲሆኑ አሳምነው ደበሌን ኢትዮጵያ ሰየመች። እርሳቸው ዋና ቆንስል ሆነው መሾማቸው ወደአገሪቱ ከሚፈልሱ አዳዲስ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቁጥር መጨመር ጋር ተገጣጠመ። ኢትዮጵያውያን ዜጎች ህይወታቸው እያለፈ ስለመሆኑ በርከት ያሉ ዘገባዎች መቅረባቸውን ተከትሎ፥ አደም ኑርሁሴን ከመክዳታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በ2008 እ.ኤ.አ. ከአዲስ አበባ ወደ ሊባኖስ ለሥራ የመሔድ ሁኔታ ተከለከለ። ይህ ክልከላ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ ሊባኖስ ተሰድደው እንዳይሰሩ ለመከልከል ከተደረጉ በርካታ ግን ሁሉም ውጤታማነት ከጎደላቸው ሙከራዎች የመጀመሪያው ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ክልከላውን ለማስፈጸም ያደረገው ጥረት አነስተኛ በመሆኑ፥ ሰውን በሕገወጥ ለሚያዘዋውሩ ሰዎች ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል። እነዚህ አዘዋዋሪዎች በስተመጨረሻ ህይወታቸው ያለፉ እና የአስከፊ ጥቃት ሰለባ የሆኑ በርካታ ኢትዮጵውያንን ወደሊባኖስ ለማፍለስ ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸውን ቀጠሉ።

ዋና ቆንስል አሳምነው ደበሌ በቆንስላው ላይ የተጋረጡትን አደጋዎች ወዲያውኑ ተገነዘቡ። በየዕለቱ የሚደርሱት የጥቃት፣ የራስን ማጥፋት እና ከመከራቸው ለመሸሽ ሲሉ ከረዣዥም ህንጻዎች ላይ ራሳቸውን በመፈጥፈጥ ሆስፒታል የሚገቡ ሴቶች ዘገባዎች በ2012 እ.ኤ.አ. የተጠናቀቀውን የሥራ ዘመናቸውን በአጭሩ የሚያመለክቱ ክስተቶች ናቸው። ዛሬ ላይ ጡረታ ወጥተው እንኳን በቤሩት ስለነበራቸው ጊዜ መልካም የሆነ ትዝታ እንደሌላቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ግልጽ አድርገዋል።

‹‹እንቅልፍ መተኛት አልችልም። በየሣምንቱ የስታፍ አባላት በሬሳ ክፍል ያሉ የዜጎቻችንን ሬሳዎች መመልከት አለባቸው። በየቀኑ ስልኮቻችን እየተደወለ የምንሰማው የሚያለቅሱ ሴቶችን ነው፤ የልባቸውን ዘክዝከው ነግረውን እንድንደግፋቸው ይለምኑናል። መከታተል እስከኪያቅተን፤›› በማለት የቀድሞው ዲፕሎማት በስልክ ነግረውናል።

በተቋምነት እጁን ለማስገባት ቸልተኛ እንደሆነ የሚታማው ቆንስላ ዜጎቹን ለመደገፍ በአቅሙ ያደረገው ነገር ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። በአሳምነው ደበሌ የዋና ቆንስልንት ዘመን ነው አለም ደጫሳ የተባለችው ሰራተኛ የሊባኖስ የሥራ ቅጥር ወኪል በሆነ አሊ ማህፉዝ እጅ ፀጉሯ እየተነጨ፣ እየተጎተተች፣ እየተደበደበች መኪና ሥር የተጣለችበት ቪዲዮ በካሜራ ተቀርጾ ርዕስ ሆኖ የነበረው። እርስዋም ቆይታ ራሷን እንዳጠፋች ተዘግቦ ነበር። በተለይም በካሜራ የተቀረጸው በደል የደረሰው በቆንስላው ፊት ለፊት መሆኑን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእርስዋን ህይወት ለመታደግ ባለመቻሉ ዋና ቆንስሉን ሲወቅሱ ነበረ

ዳሩ ግን፥ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ስልጣን እንዳልነበራቸው አሳምነው ይናገራሉ። ‹‹ወደዚያ መድረሴን ተከትሎ ወዲያውኑ የተረዳሁት እኔ ለስሙ የተቀመጥኩኝ መሆኑን ነው። መንግስት በዚህ ደረጃ ለሚያጋጥም ነገር የሚሆን ገንዘብም ሆነ ግብዓት አልመደበልንም።››

‹‹በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር በእኔ የስልጣን ዘመን የሚገባውን ያህል ትኩረት አልተደረገለትም።። እንዲሁ ረዳተቢስ እና የተጣሉ ነበሩ። ››

ጥቃት ያመለጡ ኢትዮጵያውያን ዜጋ ሠራተኞች በቤሩት የማህበረሰቡ መጠለያ ያርፉ ነበረ። ምግብ፣ ንጽህና መጠበቂያ እና ሌሎች ፍላጎቶቻቸው እስከዛሬም ድረስ የሚሸፈኑት በማህበረሰቡ ነው እንጂ በቆንስላው አይደለም (ምስል፡ ኦፕን ዴሞክራሲ)

ከላይ በስተግራ ካሉት ወደቀኝ በተራ፡ አገሬ ማንደፍሮት፣ ደስታ ታፈሰ፣ ወይንሸት አራጌ እና ትዕግስት በላይ፤ ሁሉም ወደሊባኖስ ለሥራ የሔዱት 2019 ... ነው። ማናቸውም በህይወት ወደኢትዮጵያ አልተመለሱም።

የቀድሞው ዋና ቆንስል እንደሚናገሩት ከሆነ፥ ከማህበረሰቡ ጋር አብረው ይሰሩ ነበረ፥ እናም በአቅማቸው በጊዜው ለማድረግ የቻሉትን ያህል አድርገዋል። ይህም የጎደለውን $ 640,000 ለማፈላለግ ጥረት በማድረግ መተባበርን ይጨምራል።

‹‹ምርመራ አድርጌ ነበር እናም አደም ገንዘቡን ወደጅዳ እንደላኩት ለማወቅ ችያለሁኝ፥ አምባሳደር ተክለአብም መቀበላቸውን አረጋግጠዋል›› ብለዋል አሳምነው ለአዲስ ስታንዳርድ ‹‹ግን ከዚያ በኋላ ገንዘቡ ምን እንደገጠመው ቀጥተኛ የሆነ መልስ ላገኝ አልቻልኩም።››

‹‹ገንዘቡ የማህበረሰቡ ነው። በሬሳ ማቆያው በርካታ አስክሬኖች አሉን።። ይህ ገንዘብ እነዚህን አስክሬኖች ወደ አገር ቤት ቤተሰቦቻቸው ዘንድ እንዲቀበሩ ሊያስደርግ ይችል ነበር።››

ለአዲስ ስታንዳርድ የደረሰው ማህደር በቀጥታ አምባሳደር ተክለአብ ከበደን የሚጠቅስ አይደለም። ዳሩ ግን፥ አሳምነው እንደሚሉት፥ ከፍተኛ ሹም ከሆኑ እና በቅርባቸው ከሚገኙት ጋር ስልጣናቸውን ተጠቅመው የንግድ ሥራዎችን አከናውነዋል የሚባለው በዲፕሎማቶች ክበብ ውስጥ ‹‹የአደባባይ ሚስጥር›› ነው ይላሉ። ‹‹ከእኩዮቻቸው ሲተያዩ ወጣት እንደመሆናቸው ከአብዛኛዎቹ አስቀድመው ከነጥቅማጥቅም ጡረታ እንዲወጡ ተፈቅዶላቸዋል›› ይላሉ ቀድሞው ዋና ቆንስል። ‹‹ሰውዬው የሳውዲ አረቢያ ዲፕሎማት ከመሆን፥ ድንገት በዱባይ እጅግ አዋጪ የሆነ የንግድ ሥራ ማዕረግ ላይ ታጭተው ተገኙ። ይህ ዝም ብሎ አይፈጠርም!››

የአምባሳደር ተክለአብ ከበደ በዋና ቆንስልነት የነበራቸው የሥልጣን ዘመን የተጠናቀቀው በ2011 እ.ኤ.አ. ነው። እርሳቸው ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵን የንግድ ጥቅሞች ለመንግስት ወደማስተዋወቅ ሚና ተቀየሩ። በሰኔ 2011 እ.ኤ.አ. ወደሪያድ ሔደው የሳውዲ መንግስት የኢትዮጵያን የንግድ ሥራ ጥቅሞች እንዲያስከብር በሚያነሳሳው በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር በነበሩት ሐይለማርያም ደሳለኝ የሚመራየዘጠኝ ሰዎች ኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ አንድ አካል ነበሩ። ከዚያ በኋላ ወዲያውኑ በዲባይ የንግድ ምክር ቤት ተቀጥረው፥ በዚያም የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ነበሩ።

በ2016 እ.ኤ.አ.፥ አምባሳደር ተክለአብ ‹‹ኢትዮ-ዲስፖራ ግራንድ ሞል›› የተባለውን ፕሮጀክት ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሰይመው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ባለአክሲዮኖች ሆነው የሚያሰሩትን 2.6 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የግንባታ ሒደት እንዲቆጣጠሩ ተግባር ተሰጣቸው። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ትልቅ ሽፋን የሰጡት ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች አክሲዮኖች መኖራቸውን ሲያስተዋውቁ ነበረ። ግንባታው ገና የሚጀመር እንደመሆኑ ከዚያ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ምንም ግልጽ አይደለም ደግሞም ፕሮጀክቱ ያለምንም ማብራሪያ የተተወ ይመስላል።

አምባሳደር ተክለአብ 15 ዓመት ያህል በሪያድ ዋና ቆንስል ቆይተዋል። ከዚያ አስቀድሞ በካናዳ ኦታዋ ዋና ቆንስል ነበሩ ደግሞም ከአስርት ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ በቃል አቀባይነት የሰሩበት የትግራይ ልማት ማህበር የተባለው ድርጅት የካናዳ ቅርንጫፍ ላይ የቦርድ ዳይሬክተር ነበሩ።

መረጃዎቹን አሰባስበው ከዚያም በሒደት ለአዲስ ስታንዳርድ ያስረከቡት ጠቋሚ እንደሚከራከሩት፥ አንዳንዶቹን የጅዳ ቆንስላ መዛግብት ለአጭር ጊዜ ብቻ እንዳዩአቸው እና በመንግስት ሊመረመሩ የሚገባቸው ተጨማሪ የአሰራር ስህተቶች ሊጋለጡባቸው ይችላሉ። ‹‹እውነቱ ሁሉ እንዲወጣ እፈልጋለሁ። ሕዝቡ ሊያውቀው ይገባል፥›› በማለት ማንነታቸውን እንዳይጠቀስ የሚፈልጉት ጠቋሚ ተናግረዋል። ‹‹በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ኤምባሲዎች ዙሪያ ለዓመታት የተበላሹ አሰራሮች ሲደረጉ እንደከረሙ ይወራል። ምናልባት በጥልቀት ተፈትሸው ቢታዩ፥ ተጨማሪ የአሰራር ግድፈቶችን የሚያሳዩ መረጃዎች ሊገኙ ይችላሉ።››

ነብዩ ሲራክ የሚባሉት በንጉሳዊ መንግስቱ ለረዥም ጊዜ ነዋሪ እና በሳውዲ አረቢያ የስደተኞችን ስቃይ የሚያወግዝ ቀስቃሽ ጽሑፍ በመጸፍ የሚታወቁት፥ በአገሪቱ የሚገኙ ስደተኞን መከራ ለሚያብራሩ በርካታ ጦማሮች ተከታታይ ጽሑፎችን ከትበዋል። እንደነብዩ አባባል፥ በሳውዲ አረቢያ የነበረው የአምባሳደር ተክለአብ የረዥም ጊዜ የሥልጣን ዘመን በእርሳቸው ጽህፈት ቤት በአሰራር ብልሽት እና አድልዎ ሐሜቶች የታጨቀ ነበር። ከእነዚህ ሐሜቶች ስለአንዳንዶቹ ነብዩ በጥልቀት ጽፎ ነበር፥ ይህም በ2010 እ.ኤ.አ. በከተማይቱ እስራት ላይ ለሚገኙ ስደተኞች ድጋፍ እንዲሆን በጅዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ማዋጣቸውን የተመለከተ የማህበረሰብ መነሳሳቶችን ይጨምር ነበር። የዚህ የቸርነት ጥረት አመራር በቆንስላው ውስጥ በሚገኙ የገዢው ፓርቲ አባላት እንዲበተን ተደርጓል እንደሚሉት ነብዩ አጻጸፍ፥ የተሰበሰበው ገንዘብ ወደቆንስላው ሣጥን ገብቶ ጠፍቷል

‹‹ሙስና (በአምባሳደር ተክለአብ) የዋና ቆንስልነት የስልጣን ቆይታ ወቅት ተስፋፍቶ ነበር›› ይላሉ ነብዩ ለአዲስ ስታንዳርድ ሲያብራሩ። ‹‹ለቁጥር የሚያዳግቱ ገጠመኞች አሉ፤፤ የዛሬ አስራ ሦስት ዓመት አከባቢ ኢትዮ-ሳውዲ ትስስርን ለማስታወስ በሚል በኢትዮጵያ ሐውልት ለመስራት ተብሎ የተዋጣ 100,000 የሳውዲ ሪያል (ወደ$26,000 የአሜሪካ ዶላር ያህል) የሆነ በግላጭ ተዘርፎ ያውቃል።። ሐውልቱም አልተሰራም ገንዘቡም የት እንዳለ አይታወቅም።››

ዋና ቆንስል በነበሩበት ጊዜ፥ የሚድያ ትኩረትን ለማምለጥ ይፈልጉ በነበሩ ሰው ላይ እንዲህ ዓይነቱ ሐሜት የሚያስወቅስ ነው። አምባሳደር ተክለአብ ከበደ ቃለመጠይቆችን ይቀበሉ የነበረው ርዕሰ ጉዳዩ በኢትዮጵያ የንግድ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ብቻ ነበር በፍቃደኝነት የቃለመጠይቅ ይቀበሉ የነበረው። ለምሳሌ ያህል፥ በጋምቤላ ክልል በተለይም ለም በሆነ መሬት ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የመዋዕለንዋይ ፍሰት እንዲያደርጉ ለሳውዲ ነጋዴዎች ጥሪ በማድረግ ይታወቃሉ፤ ይህም ተግባር ሳይሳካ ሲቀር የአከባቢውን ቀደምት ማህበረሰብ በማፈናቀል የኢትዮጵያ መንግስት እንዲወቀስ አድርጓል።።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ውስጥ፥ አምባሳደር ተክለአብ የፓርኪንሰን ታማሚዎች ድጋፍ ድርጅት (ፒ/ፒ/ኤስ/ኦ) የቦርድ አባል ሆነው ተመዝግበው ቲ/ኬ/ኤ ኢምፖርት ኤንድ ኤክስፖርትን ጨምሮ በርካታ የንግድ ሥራዎችን ያከናውኑ ነበር። ይህ ኩባንው የግብርና ምርቶችን ለውጭ ንግድ እንደሚያቀርብ በይፋ የታወቀ ነው፤ ዳሩ ግን፥ በሌላ የንግድ ሥራዎች ዝርዝር ውስጥ ኩባንያው ከአፍሪካ ወርቅ በወቄት ወደውጭ የሚልክ ሆኖ ዕውቅና የተሰጠው ነው።።

አምባሳደር ተክለአብ ከበደን ማግኘቱ በራሱ ሌላ ስራ ነው። ከሥራ ዘርፎቹ ማናቸውም ቢሆን አድራሻቸውም ሆነ ስልካቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ አይደሉም። ‹‹ለማንም ቢሆን ስልክ ቁጥሩን አይሰጥም›› ይላሉ ነብዩ ሲራክ ሲብራሩ። ‹‹ማህበራዊ ሚዲያ አይጠቀሙም፣ ማንም ዱካቸውን ለመከተል አይችልም። በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በርካታ ችግሮች ላለመጋፈጥ ሲሉ የሚጠቀሙባቸው ስልክ ቁጥሮች ብዙ ናቸው።››

በተቃራኒው፥ በጊዜ ሒደት የቅርባቸው የሆነ የሚታመን ሰው በቀድሞው ዲፕሎማት እጅ የሚገኙ ስልክ ቁጥሮችነን ዝርዝር አውጥቶ ለአዲስ ስታንዳርድ ሰጥቷል። አምባሳደር ተክለአብ በስልክ በመገኘታቸው የተደናገጡ ቢሆንም፥በሚያስደንቅ ሁኔታ ከአወዛጋቢው የ2009 እ.ኤ.አ. የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዙ ጥያቄዎችን ለመመለስ ግን መስመሩን ሳያቋርጡ ቆይተዋል።

ገንዘቡ በመጀመሪያ ከቤሩት ወደጅዳ በተላለፈበት ጊዜ እና ለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር በተከፈለበት በ2009 እ.ኤ.አ. ጭምር እርሳቸው የጅዳ ቆንስላ ኃላፊ የነበሩ ሰው ናቸው። ዳረ ግን ስለእነዚህ ጉዳዮች በተጠየቁ ጊዜ ስለእነዚህ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ክደዋል። ‹‹ስለምንድነው የምታወራው›› ነበረ ምላሻቸው።

‹‹በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች አንዳንድ ጊዜ ከአንዳቸው ጽህፈት ቤት ወደሌላኛው ገንዘቦችን ያስተላልፋሉ፤›› ብለዋል አምባሳደር ተክለአብ ከበደ። ‹‹ዳሩ ግን ከሊባኖስ ወደሳውዲ አረቢያ የተደረገው የገንዘብ ዝውውር ያልተፈጠረ ነው። ደግሞም ወደ አሜሪካ ብር ስለመላኩ የሚወራውም ውሸት ነው።›› ይህንን የሚቃረን መረጃ በአዲስ ስታንዳርድ እጅ እንደሚገኝ በተነገራቸው ጊዜ ቀለል ባለ ሁኔታ ‹‹ስለእንደዚህ ዓይነት ነገር የሰማሁት የለም፥ የእኛ የአሰራር ፕሮቶኮል ጋር የሚጋጭ ነው›› ብለዋል።

ነገር ግን፥ አምባሳደር ተክለአብ ዘለግ ላለ ጊዜ ለመነጋገር ፍቃደኛ ነበሩ፤ ይህም በኢትዮጵያ የሚገኙ ሹማምንት እንደእነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን ደፋፍኑ ከመሆኑ ጋር ሲስተያይ ይበል የሚያስብል ነው። ስለጉዳዩ ይበልጥ በተነጋገሩ ቁጥር፥ ያላቸው አቋም በሒደት እየተቀየረ ነበረ። በሒደትም በሊባኖስ የሚገኝ ዲፕሎማት ጓዳቸውን ስም ጠርተው ከሊባኖስ ገንዘቡ በተላለፈ ጊዜ በጅዳ የማህበረሰቡን ገንዘብ የተቀበሉ ብለው ጠቁመዋል። ከዚያም በዚያን ጊዜ ላይ ይህ ዕውነት እንደማይሆን የተናገሩ ቢሆንም ዋና ቆንስል አሳምነው ደበሌ ዋሽተዋል ማለታቸው እንደሆነም ተጠይቀው ነበረ።

‹‹እንደዚያ አላልኩም›› አሉ አምባሳደር ተክለአብ አሁን ‹‹አላስታውስም ነው ያልኩት። በጣም እርግጠኛ ሆኜ ግን ምንም ገንዘብ ወደ አሜሪካ እንዳልተላከ መናገር እችላለሁ። ከቤሩት ወደጅዳ ገንዘብ ተልኮ ሊሆን ይችላል። በሁለቱ ቆንስላዎች መካከል የሥራ ግንኙነቶች ነበሩ። በጽህፈት ቤቶች መካከል ገንዘብ መላላክ የተለመደ ነው። ዳሩ ግን ገንዘብ አሜሪካ ያለ ድርጅት ስለመላኩ የሚወራው ግን ሐሰት ነው።››

አዲስ ስታንዳርድ፡- ‹እንግዲህ መጠኑ $640,000 የሆነ ገንዘብ ከቤሩት ወደጅዳ ተላልፎ ሊሆን ይችላል ማለት ነው፤››

አምባሳደር ተክለአብ፡- ‹‹ሊሆን ይችላል፤ አላስታውስም፥ ግን ሆኖ ይሆናል። በጣም ትልቅ መጠን ያለው ገንዘብ ነው ምንላላከው፤ እናም እያንዳንዱን ሐዋላ ማስታወስ በጣም ይከብደኛል። ዳሩ ግን፥ በጣም እርግጠኛ ሆኜ ልናገር የምችለው ወደ አሜሪካ የተላከ ገንዘብ እንደሌለ ነው። ደግሞም በዚህ ዓይነት መንገድ የተደረገ ገንዘብ ቢኖር በአዲስ አበባ ካሉ የበላዮቼ ጸድቆ የተደረገ ነው።››

አዲስ ስታንዳርድ፡- ‹‹በጅዳ ቆንስላ ከሚገኙት መካከል እርስዎ ሳያውቁት ገንዘቡን ወደ አሜሪካ እንዲተላለፍ ሊያደርጉ የሚችሉበት ዕድል አለ?››

አምባሳደር ተክለአብ፡- ‹‹የለም፥ ሊሆን አይችልም፤ ሁሉም ነገር የሚሆነው በእኔ ሥር ነው። የፋይናንስ ሹም አለን፤ ዳሩ ግን ወደጅዳ የሚገባውን እና የሚወጣውን ማንኛውንም ነገር የምፈቅደው እኔ ነበርኩ። ለዚህም ነው ይህ ሐሜት ሐሰት ነው ብዬ በእርግጠኝነት የምናገረው።››

‹‹የምታሳትሙትን ነገር ተጠንቀቁ›› ብለዋል ሲያስጠነቅቁን ‹‹ይህ ሐሜት ፈጠራ ነው። ሙያችሁን ለኪሳራ ትዳርጉታላችሁ።››

Zecharias Zelalem on Twitter: "The misappropriation of $640,000 belonging  to maids in Lebanon by Ambassadors Nega Tsegaye & Tekleab Kebede, was kept  secret. Both ...Zecharias Zelalem on Twitter: "Transfer was completed by Ethiopia's consul  in Jeddah, Ambassador Tekleab Kebede Aregawi. According to residents, Amb.  Tekleab's 15 ...

አምባሳደር ተክለአብ ከበደ አረጋዊ

ዳሩ ግን፥ በአዲስ ስታንዳርድ እጅ የሚገኙት ሰነዶች የሚያመለክቱት በተቃራኒው ነው። ከተረጋገጠው ሰነድ በግልጽ እንደሚታየው፥ በማህበረሰቡ ሒሳብ የሚገኘው ገንዘብ ነበር ወደአሜሪካ የተላከው። ደግሞም አምባሳደር ተክለአብ ራሳቸው እንዳመኑበት፥ እርሳቸው ሳያውቁት በ2009 እ.ኤ.አ. ለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የተደረገው ክፍያ ሊፈጸም አይችልም። እንግዲህ፥ የእርሳቸው ስም በሰነዱ ላይ ባይኖርም፥ እርሳቸው ያላቸውን ስልጣን ማስተባበል ለግምት ይከብዳል። ነገር ግን፥ የበላዮቻቸው ስለመሳተፋቸው እርሳቸው የተናገሩት ነገር ውስጥ የተወሰነ ዕውነት ያለ ይመስላል።

ለወራት አዲስ ስታንዳርድ ሲመረምራቸው ከቆዩ ሰነዶች መካል፥ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጅዳ የተላከ የፋክስ ሰነድ አለ። በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሹም የተላከው ደብዳቤ ዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር ለተባለው ድርጅት የባንክ ሒሳብ ወደባልቲሞር ባንክ በአሜሪካ ዶላር $600,000 እንዲተላለፍ የሚጠይቅ ነበር።

 

 

ይህ ደብዳቤ በኤምኤንድ ቲ ባንክ ቅርንጫፍ ያለውን የዲ/ኤል/ኤ ባንክ ሒሳብ መረጃዎች የያዘ ነው። ይህም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፋይናንስ መምሪያ ሹም፥ በማስከተልም በፈረንሳይ እና ስፔይን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ባገለገሉት አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ የተፈረመበት ነው። በዲፕሎማትነት የሥራ መስክ፥ አምባሳደር ነጋ አሁን ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ዲፕሎማሲ ማስተዋወቂያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ከአምባሳደር ተክለአብ በተቃራኒው፥ አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ ስለጉዳዩ ለመነጋገር ፍቃደኛ አልነበሩም። ‹‹ስለምን እንደምታወራ አላውቅም›› የሚል ነበር ከአዲስ ስታንዳርድ በስልክ ሲጠየቁ ምላሻቸው። ‹‹የጠየከኝ ነገር ከአስር ዓመት በላይ ጊዜ ያለፈው ነገር ነው። እንደዚህ ዓይነት ነገር በስልክ ማውራት ተገቢ አይደለም።››

ለታሪኩ ጉዳዩን ይበልጥ ለማውራት በኢሜል ግንኙነት ለማድረግ ፍቃደኛ ይሆኑ እንደሆነ ተጠይቀው፥ ድምጻቸው ይበልጥ ቁጣን ቀላቀለ፡ ‹‹ቀጥሉ! የፈለጋችሁትን አሳትሙ። አሁን ቢሮዬ ውስጥ ከሰው ጋር ነኝ። ይቅርታ፤›› ከዚያ ስልኩ ተቋረጠ።

Image

አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ

ከአምባሳደር ተክለአብ በተቃራኒ፥ የእርሳቸው ፊርማ እና ስም በሰነዱ ላይ በግልጽ የሚታይ ሲሆን፥ ሕዝቡን ስላሞኘው ገንዘብ ዝውውር ቀጥተኛ ተሳታፊነታቸውን የሚያመለክቱ ናቸው።

/ኤል/ ፓይፐር (DLA Piper)

የዚህ ታሪክ ማዕከል የሆነው የሎቢ ድርጅት የሚያደናግር ቅድመታሪክ ያለው ነው። የኢትዮጵያ መንግስት እና ዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የሚነገርላቸው የሚባለው ስኬት ኮንግረሱ ኤችአር 2003 ወይም የ2007 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እና ተጠያቂነት አዋጅ እንዳይወጣ በተሳካ ሁኔታ ለማደናቀፍ ኋለኛው በሰራው ስራ ነው። ይህ አዋጅ ኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ኩነቶች የአሜሪካ መንግስት እንድትወቅስ በመጋበዝ ማዕቀቦች እንዲጣሉ፥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው አንጋፋ ኢትዮጵያውያን ሹማምንት ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መከለከልን ይጨምራል። ዳሩ ግን፥ የዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር ሰራተኞች ጥሰው በመሔድ፥ በሽብርተኝነት ላይ ለሚደረገው ጦርነት ኢትዮጵያ ጠቃሚ አጋር እንደምትሆን የሚገልጹ ፓምፍሌቶችን በማዘዋወር የሪፐብሊካንኖችን ተሳትፎ ገበዩ። አንዳንድ አሜሪካዊ ኢትዮጵያውያን ቀስቃሾች የሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረት ቢኖርም፥ የሰብዓዊ መብቶች ሙከራዎች ተዳፈኑ።

በ2006 እ.ኤ.አ. ዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር በየወሩ ንጹህ የ$50,000 ክፍያ ያገኝ የነበረ ሲሆን፥ ይህም በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ለሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የማማከር እና ይፋዊ ሎቢዪንግ አገልግሎት ብቻ የሚከፈል ነበር። ጋሪ ክሌይን የተባሉት የዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር ቃል አቀባይ ለዶቼ ቬሌ አማርኛ ቋንቋ ፕሮግራም ሲናገሩ፥ ኢትዮጲያ ከ2005 እ.ኤ.አ. የምርጫ ብጥብጥ በፊትም ሆነ በኋላ የፖለቲካ እስረኛ እንዳልነበራት በመናገር አስደንግጠዋል። ከክሌን አስተያየት የተነሣ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ትልቅ ቁጣ ተቀስቅሶ ስለነበር፥ ቢያንስ በአንድ አጋጣሚ በዋሽንግተን ዲሲ ጽህፈት ቤት የሕግ ድርጀቶች ፊት ለፊት ተቃውሞ ተደርጎ ነበር።

ጋሪ ክሌን የተባለው የአሜሪካ የሎቢ ድርጅት /ኤል/ ፓይፐር ሠራተኛ፥ በኢትዮጵያውያን ዘንድ 2005 ... ኢትዮጵያ ምርጫ ተከትሎ እና አስቀድሞ የፖለቲካ እስረኛ እንደሌላት ለኢትዮጲያዊ ሬድዮ አዘጋጅ በመናገር በኢትዮጵያውያን ዘንድ ይታወሳል፤ (ምስል፡ ብሉምበርግ)

/ኤል/ ፓይፐር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት የሚቃወም መልዕክት የያዘ ፖስተር (ምስል፡ ዳንኤል ኒሃውሰር)

Image

አንድ በአሜሪካ ነዋሪ የሆነ የታክሲ ሹፌር የዲኤል ኤ ፓይፐርና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተደረገው የስራ ስምምነት በዚህ መልክ ተቃውሞዉን አሳይቶ ነበር

የሰብዓዊ መብቶች ቀስቃሾች እና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተቃዋሚ ኃይሎች ቁጣ ያረፈበት ሲሆን ብዙ ስም መጉደፍም ደርሶበታል። በሚያዝያ 2009 እ.ኤ.አ.፥ ብዙ ጫና ስለነበረበት በሚመስል ሁኔታ ‹‹በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት›› ተብሎ ከሚጠራው ጋር በተያያዘ ያለውን ሥራዎች የሚያበቃ መሆኑን አሳውቋል። ኩባንያው በበርካታ የኢትዮጵያ መረጃ ምንጮች፥ ኦፕረይድ ዶት ኮምን ጨምሮ፥ ተወስዶ ዳግም የተሰራጨ መግለጫ አውጥቷል። በስተመጨረሻ ባወጣው ማሳሰቢያ፥ ድርጅቱ በለንደን እና በብራሰልስ እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ ‹‹ከ(ኢትዮጰይ መንግስት) መስራቱን›› ጠቅሷል።

በአዲስ ስታንዳርድ እጅ የሚገኙ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የተከፈለው ከሊባኖስ የማህበረሰብ ፈንድ የተመዘበረ መሆኑን የሚያሳይ እና መግለጫው ይፋ በሆነ በሣምንት ጊዜ አከባቢ የወጣ ነው። ሰነዱ ግልጽ እንደሚያደርገው ከላይ በዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር ከተሰጠው በሰፊው ይፋ የተደረገ መግለጫ ጋር በሚገርም ሁኔታ የሚገጣጥም በሆነ ሁኔታ በለንደን፣ ብራሰልስ እና ዋሽንግተን ዲሲ ካሉት የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ጋር ለተሰራው ሥራ ለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የተከፈለ ገንዘብ መሆኑን ነው።

ለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የሚዲያ ቃልአቀባዩን ጆሽ ኤፕስተን በስልክ ለማግኘት ከአዲስ ስታንዳርድ የተደረገው ሙከራ መልስ አላገኘም፤ የኢሜይሉን ጨምሮ።

ባንኴ ሳውዲ ፍራንሲ መጠኑ $600,000 ዶላር የሆነ ገንዘብ ከጅዳ ቆንስላ ለዲ/ኤል/ ፓይፐር የተላለፈበት ደረሰኝ፤

በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጰያውያን አስርት አመታትን ያስቆጠረ ብዥታ

በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፥ በቆንስላው እና በማህበረሰቡ አባላት መካከል ስብሰባዎች በተደረጉ ቁጥር የሚገነፍል ተስፋ መቁረጥ ተደጋጋሚ ምክንያት የነበረው የገንዘቡ መጥፋት ነበር። ሕይወት ይህንን ስታስታውስ ይህ ያልተቋረጠው ውጥረት ምክንያት እንደሆነ በማስረዳት ነው።

‹‹ሊባኖስ ውስጥ ሴቶች ያለመቋረጥ ሲደበደቡ እና ተገድደው ሲደፈሩ ነበር።›› ይላሉ ህይወት ሲናገሩ፤ ‹‹የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በራሱ ገንዘብ የጥቃት ሰለባዎችን ለማስጠለል መጠለያ ከፈተ። ቆንስላው ወጪውን ለመሸፈን እርዳታ አላደረገልንም፤ እኛም በራሳችን ስንፍጨረጨር ነበር።››

ሕይወት እንድሚናገሩት፥ ያላቸውን ሁሉ አሰባስበው አነስተኛ ሁለት ክፍል አፓርታማ ተከራይተው በመጠለያነት ለመጠቀም ለሚገደዱት በማህበረሰቡ ውስጥ ለሚገኙ በጎ አድራጊዎች ገንዘቡ ብዙ ልዩነት ይፈጥር እንዲሁም ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረው ነበረ። የማህበረሰቡ ንብረት የሆነውን ነገር እንዲመልስ ለቆንስላው የሚደረገው ጥያቄ ምርመራ ለማድረግ ቆንስላው ምንም ፍቃደኝነት ሳያሳይ በቀረ ቁጥር ግለቱ ጨምሮ አረፈው።

መሠረት ወርቅነህ፥ ገንዘቡ መጀመሪያ ከቤሩት በተዛወረበት ጊዜ ላይ የማህበሩን ገንዘብ ነክ ሁኔታዎች ከሚንከባከቤ ዐቃቤ ነዋዮች መካከል እንደመሆናቸው፥ የዚህን ጉዳይ ጥግ ምን እንደሚሆን ለማየት የግል ተልዕኮ አድርገውት ነበር።

‹‹ከአምስተኛ ፎቅ ላይ የወደቁ የአገሬ ሠራተኞች የሚገባቸውን የጤና እንክብካቤ ለማግኘት አቅም አጥተው ሳይ ደሜ ይፈላ ነበር። እግራቸውን ተሰብረው የተረፉ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ክራንች ለመግዛት አቅም ሰለሌላቸው ከሆስፒታል ሲወጡ ጓደኞቻቸውን ተመርኩዘው ነው።››

እርሳቸው በጉዳዩ ላይ ያለማቋረጥ ሲነዘንዙ ስለነበረ በኢትዮጰያ መንግስት ዓይን ውስጥ ገብተው እንደነበረ ያምናሉ።

‹‹መጀመሪያ ላይ የማህበረሰቡ አመራር ውስጥ ያለኝን የሥራ ማዕረግ አጥቻለሁ፤›› በማለት መሠረት ያስታውሳሉ፤ ‹‹ከዚያም ወቅቱን ጠብቄ ለቆንስላው የእድሳት ሰነዶቼን ያቀረብኩኝ ቢሆንም የመኖሪያ ፍቃድ ወረቀቶቼ ጊዜያቸው አልፎበታል። የመኖሪያ ወረቀቶች ስላልነበሩኝም፥ የሊባኖስ ፖሊስ አስሮኝ ለሁለት ቀናት ያህል እስር ቤት ነበርኩኝ። በቆንስላው ከሚገኙት አንዳቸው በቅጣት የዕድሳት ማመልከቻዬን እንዳስቀሩብኝ እርግጠኛ ነኝ።››

በአሳምነው ደበሌ የስልጣን ዘመን ይላሉ መሠረት፥ በቤይሩት የሚገኘው ቆንስላ ጉዳዩን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይበልጥ ይቀበል ነበር። ‹‹እኔ አሳምነውን አልወቅሳቸውም። ጉዳዩን ተምልከተዋል፤ ዳሩ ግን፥ ዝም እንዲሉ አስፈራርተዋቸው ይሆናል። እየዞረ በመጠየቁ ጡራታቸውን አደጋ ላይ ጥለዋል።››

በግንቦት 2012 እ.ኤ.አ. ከሁለት ወራት በፊት አለም ደጫሳ በሚያሰቅቅ ሁኔታ ህይወቷ በማለፉ በተፈጠረ ተቃውሞ፥ ኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ ጉዳይ የሴቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት ልዑክ በመመደብ በዚያ የሚገኙ ዜጎችን ቸል ብለዋል የሚባለውን ሐሜት ለማስቀረት በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አግኝተው ነበር። ቆይተው የኢትዮጵያ የሴቶች ጉዳይ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ፍሬህይወት አስራት የልዑኩ አንድ አካል ሆነው ወደቤሩት ከሔዱት መካከል ይገኛሉ።

በማህበረሰቡ አባላት እና በመንግስት ሹሞች መካከል የተደረገውን ስብሰባ ቃለጉባዔ የያዘ እና በማህበረሰቡ ተዘጋጅቶ በጠረጴዛው ዙሪያ በነበሩ ተሳታፊዎች የተፈረመ ቃለጉባኤ ሰነድ ለአዲስ ሰታንዳርድ ደርሶታል። ይህም የተረባበሸ ነበር የሚባል መሆኑን ያሳያል። የማህበረሰቡ አባላት ቆንስሉን ላደረገው ድርጊት ሰድበውታል።። ሌሎች ደግሞ ለአለም ደጫሳ ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። መሠረት ወርቅነህ፥ በዚያን ጊዜ የማህበረሰቡ የገንዘብ ክፍል ኃላፊ የነበሩት በስብሰባው ወቅት በሙስና ተከሰዋል፥ የእርሳቸው የመኖሪያ ወረቀት ሆን ተብሎ ግዜው እንዲያልፍ የተደረገበት ምክንያትም እንዲሁ ተመርምሯል።

በርካታ የሙስና ውንጀላዎች በነበሩበት፥ የጎደለው የማህበረሰቡ ፈንድም እንዲሁ ተነስቷል።። ‹‹ወደሳውዲ አረቢያ ከመላኩ አስቀድሞ በድምሩ $640,000 ያህል ገንዘብ ለማዋጣት ችለን ነበር። ይህ ገንዘብ የት ነው ያለው? ››

የማህበረሰቡ ተወካይ፥ ገንዘቡ ሊመለሰስ ስለመቻሉ ተስፋ እንደሌላቸው የተሰማቸው በሚመስል ሁኔታ ‹‹ምናልባት ገንዘቡ ካለ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በልገሳ ይሰጥልን ዘንድ እንጠይቃን›› ብለዋል።

በግንቦት 2012 ... በመንግስት ሹማምንት እና በሊባኖስ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት መካከል በጠረጴዛ ዙሪያ የተደረገ ውይይት ሪፖርት፤

በዚህ ሰነድ ውስጥ በማህበረሰቡ ተወካዮች፣ በቆንስላው ስታፍ እና በዜጎች መካከል የተካረረ የቃላት ምልልስ እንደነበረ ያሳያል። ፍሬሕይወት አስራት በጠብ ላይ የሚገኙ አካላትን ለማሸማገል ስትሞክር እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን፥ ሪፖርቱ ግን የትኛውንም ሐሜት ቢሆን መልስ ለመስጠታቸው የሚጠቅሰው ነገር የለም።

መሠት ወርቅነህ፥ ስለጠፋው ገንዘብ መጠየቅ እንድታቆም ጫና ይደረግባት የነበረ በመሆኑ፥ ሰነዶችዋ ጊዜያቸው እንዲያልፉ የቆንስሉ ስታፍ ማድረጋቸውን በመወንጀልዋ ታስራ፥ ተስፋ አልቆረጠችም። በዚያ ዓመት ቆየት ብሎ፥ ወደ አዲስ አበባ በመሔድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፋይናንስ መምሪያ እንዲሰሟት ጠይቃ ነበር። ዳሩ ግን አለመታደል ሆነና፥ እዚያ የገጠማት ሌላ ሳይሆን አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ ነበረ።። በዚያን ጊዜ፥ ከገንዘቡ መጥፋት በስተጀርባ እርሱ እንዳለበት አላወቀችም ነበር።.

‹‹ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀርቤ ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር በላይ የልገሳ ገንዘብ እንዳጣን ነገርኳቸው›› በማለት ታስታውሳለች። እርሷ እንደምትነገረው ከሆነ፥ የፈረንሳይ አምባሳደሩ ቁጣቸው ነድዶ ነበር።

‹‹በጣም ተቆጣ። እኔ የጠየቅኹትን ጉዳይ እንዲታይ ለማድረግ፤ ለእያንዳንዱ ልገሳ ደረሰኞችን ማቅረብ አለብኝ። የተለገሰውን 640,000 ዶላር የሚያሳይ ደረሰኝ! ጉዳዩን ለማየት ፍላጎት እንደሌለው ግልጽ ሆነልኝ። ››

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች ትብብር እንደማያደርጉ ግልጽ በሆነ ጊዜ፣ መሠረት ታደርግ የነበረውን ፍለጋ ማቆሟን ትገልጻለች። ከዚያ ነጥብ በኋላ ዋጋ ቢስ መሆኑን አመነች።። ከገንዘቡ መጥፋት ጀርባ የአምባሳደር ነጋ ጸጋዬ እጅ እንዳለበት ሲነገራት፥ መሠረት አለማመኗን ገልጻለች። ‹‹አሁን ገና ገባኝ›› ትላለች መሠረት ለአዲስ ስታንዳርድ። ‹‹ይህንን ጉዳይ በቢሮው ላለ ሌላ ሰው አውርቼው ቢሆን ኖሮ፥ ነገሮች ለውጥ ይኖራቸው ነበረ።››

ከመሠረት ጋር የተጋፈጠውን ተከትሎ፥ የተቆጣው የቀድሞ የስፔይን አምባሳደር ለዋና ቆንስል አሳምነው ደበሌ ደወለ።

‹‹በጣም ተቆጥቶ ነበር። “እኔ ዘንድ ለምን ላክሃት?” አለኝ እኔም እንዳልላክኋት ለማስረዳት ሞከርኩኝ፤ ሊሰማኝ አልቻለም›› ይላል አሳምነው የስምንት ዓመቱን ታሪክ በዝርዝር ሲያስታውስ። ‹‹የመሠረትን አፍ አስዘጋ፣ በቃ በዚያው ቀረ።››

መንግስታዊ ዝምታ

ጊዜያት ሲያልፉ እና በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያ ዜጋ ሰራተኞች ምንም ለውጥ አለመኖሩን ሲያስተውሉ፥ በሊባኖስ ውስጥ ነገሮችን ለማስተካከል ጥቂት አዳዲስ የለውጥ ዕድሎችን ሊፈጥር የሚችለው አዲስ ዲፕሎማቶች ተሾሙ። አምባሳደር ሐሊማ መሐመድ፥ ሥራቸውን በዲፕሎማትነት የጨረሱት፥ የቀድሞ የጣልያን አምባሳደር አዲስ ዋና ቆንስል ሆነው ተሰየሙ። የኦሮሚያ ክልል የባህል እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በዘጠናዎቹ ይሰሩ ነበረ። ሴት እንደመሆናቸው፥ አንዳንዶች ከቀዳሚዎቻቸው ይልቅ ይበልጥ ጥቅምን ያስከብሩ ይሆናል ብለው ያምኑ ነበር። በቤሩት እስከ 2017 እ.ኤ.አ. ቆይተዋል።

አምባሳደር ሐሊማ መሃመድ

አምባሳደር ሐሊማ አሳምነው ደበሌን ከመሣሠሉት የተሻለ ውጤታማ በመሆናቸው ይታወሳሉ። በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ መካከል የሚገኝ አንድ ቀስቃሽ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው፥ ከቀዳሚዎችዋ በተቃራኒው፥ አምባሳደር ቅን የሆነ ጥረት በማድረግ በሊባኖስ ያለው ችግር እንዲፈታ ሞክረዋል። ስለጎደለው የ$640,000 የአሜሪካ ዶላር ጉዳይም መጨረሻውን ለማግኘት ጥረት አድርገው ነበረ።

ጥቆማ ያደረሱን ግለሰብ ማስረጃዎችም ይህንን ዕውነታ የሚያጸና ነው። በጅዳ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስል የተላከ የሚመስል እና ከቤይሩት አቻው በገንዘቡ ጉዳይ ስለተፈጠረው ነገር ሙሉ ማብራሪያ እንዲሰጠው ለቀረበው ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ ያለበት የፋክስ ሰነድ በአዲስ ስታንዳርድ እጅ ይገኛል።

ቀኑ ሰኔ 19/2008 ዓ.ም የሆነው ይህ ደብዳቤ እንደሚያሳየው በቤይሩት ያለው የኢትዮጵያ ቆንስል፥ በውቅቱ በአምባሳደር ሐሊማ መሐመድ የሚተዳደር እንደመሆኑ፥ በሊባኖስ የኢትዮጰያውያን ነዋሪዎች ዕይታ፥ የተዘጋ ማህደር ለሚባለው ጉዳይ ጥያቄዎችን ያነሳ ነበረ። አምባሳደር ተክለአብ ከበደ ከጅዳ ከወጣ አምስት ዓመት ሆኖታል። ደብዳቤውም በአዲሱ ዋና ቆንስል አምባሳደር ውብሸት ደምሴ ፊርማና ይፋዊው የቆንስል ማህተም የተደረገበት ነው።

‹‹በሰኔ 2/2008 . በተጻፈው ደብዳቤ መሠረት፥ የእኛ ሚስዮን በወቅቱ በሊባኖስ ከነበረው አለመረጋጋት የተነሣ በአስቸኳይ እርምጃነት ከቤይሩት ተተቀማጭ የተደረገው ገንዘብ የት እንደደረሰ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር።››

አምባሳደር ውብሸት በዚያው ደብዳቤ ውስጥ ቀጥለው ሲያረጋግጡ ማህደር ውስጥ ከቤሩት ወደጅዳ $640,000 የአሜሪካ ዶላር መላኩን ያሳያል። ደብዳቤው ቀጥሎ ሲያብራራ፥ መጠኑ $600,000 የአሜሪካ ዶላር ወደዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር ሚያዝያ 9/2001 ዓ.ም መተላለፉን ተከትሎ፥ ከዋናው መጠን ላይ $39,895,00 የሆነ ገንዘብ ብቻ እንደቀረ ይገልጻል።

ይህም መልዕክት በዋሺንግተን ዲሲ አሜሪካ፤ በለንደን እንግሊዝ፤ እና በብራሰልስ ቤልጅየም ለሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የምክር ጊዜያት ወጪዎችን ለመሸፈን እንዲሆን ገንዘቡ ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን ከሌሎች ሰነዶች እኩል ሲያብራራ እናገኘዋለን።

ይህ ሰነድ የሚያጋልጠው ነገር በኖር፥ እርሷ እንድታገለግል የተሾመችላቸው ሴቶች ንብረት የሆነ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደ ዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር እንዲተላለፍ የመደረጉን ዕውነታ አምባሳደር ሐሊማ መሐመድ ያውቁ እንደነበረ ነው። በአምባሳደር ውብሸት ደምሴ ይመራ የነበረውና በጊዜው የጅዳ ቆንስላ ከነበረው ለእርሷ መስሪያ ቤት የተላከው መልዕክት በሰኔ 2016 እ.ኤ.አ. ላይ የማህበረሰቡ ገንዘብ ምን እንደደረሰበት አምባሳደር ሐሊማ ያወቁ መሆኑን በተጨማሪነት ያስረዳል። ዳሩ ግን፥ ዕውነታውን በሊባኖስ ለሚገኙ እና ከሰባት ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ጥያቄው ለሚያንገበግባቸው ኢትዮጵያውያን ዕውነቱን አልገለጡም ነበር። በማስከተል ዝምታን መምረታቸው ግር የሚል ነው።

አምባሳደር ሐሊማ፥ በአሁኑ ሰዓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስነምግባር ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ፥ በወቅቱ ለምን እንዳላጋለጡ ማብራሪያ ተጠየቁባቸውን የአጭር መልዕክት እና የድምጽ ጥሪዎች ምላሽ አልሰጡም።

የደብዳቤውን ባለንብረት ግን አዲስ ስታንዳርድ አግኝቷቸዋል። አምባሳደር ውብሸት ደምሴ፥ በጅዳ ዋና ቆንስል፥ በ2018 እ.ኤ.አ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዛውረዋል።

አምባሳደር ውብሸት ድምሴ (ምስል፡ ሳውዲ ጋዜት)

በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ የቀድሞ ሰው ስለክስተቱ የራሳቸውን ተረክ ያቀረቡ ሲሆን ይህም በርካታ ነገሮችን አጋልጧል።

‹‹እስከማስታውሰው ድረስ፥ የገንዘቡ ንብረትነት የማህበረሰቡ ነው፤ ደግሞም የገንዘብ ሚኒስቴር አያውቀውም ነበረ።›› ብለዋል አምባሳደር ሲናገሩ፥ ‹‹ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር በነበረን ስብሰባ፥ እኔ እና ሐሊማ የዚህን ገንዘብ ጉዳይ ለእርሳቸው አንስተንላቸው ነበረ።››

‹‹ስለነገሩ መረዳታቸውን ተከትሎ፥ ዶ/ር ቴድሮስ የገንዘቡ ንብረትነት የኢትዮጵያ መንግስት እንዳልሆነ እና አስፈላጊዎቹ ሒደቶች ተከናውነው ለማህበረሰቡ መመለስ አለባቸው ብለው ወሰኑ።››

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ፥ በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆናቸው፥ የኢትዮጵያ መንግስት በሊባኖስ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ገንዘብ እየመዘበረ እንደነበረ የሚያወቁት ነገር ስለመኖሩ ማስረጃችን የሚጠቁመው ነገር የለም። ዳሩ ግን አምባሳደር ውብሸት ቀጥለው ለአዲስ ስታንዳርድ በገለጹት መሠረት፥ ዶ/ር ቴዎድሮስ ገንዘቡ ተመልሶ ለማህበረሰቡ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ካደረጉ በኋላ፥ ገንዘቡ ሊመለስ እንደሚችል እና ይህ ጉዳይ ተፈትቷል ብለው ቢያምኑ ነው። አምባሳደር ውብሸት ነገሩ እንዲያ አለመሆኑ ስንነግራቸው ተደናግጠዋል። እንደሌሎቹም ዲፕሎማቶች ወደዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር የኤም/ኤንድ ቲ ባንክ ሒሳብ እንዲዛወር ስለመደረጉ የሚያውቁት ምንም ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል።

‹‹ገንዘቡ ለኢምባሲው መጠቀሚያነት በአሜሪካ ሎቢይስት ድርጅት አገልግሎት እንደዋለ በሚመለከት የሰማሁት ነገር የለም›፤፤› ብለዋል። ቆንስላው ለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር አገልግሎት ክፍያ ማድረጉን እንደሚያውቁ የሚያስረዳ ሰነድ ላይ የእርሱ ስም እና ፊርማ መኖሩን በማግኘታችን እያነጋገርነው መሆኑን ስናሳስበው፥ ቀለል በማድረግ እንደማያስታውሱ ነግረውናል።

‹‹በዚያን ጊዜ ኦዲት መደረጉን አስታውሳለሁ። ግን ይሄንን የሚገልጽ ሰነድ መፈረሜን አላታውስም።››

‹‹ኦዲት የተደረገው አምባሳደር ሐሊማ መሐመድ በጅዳ የሚገኘው ቆንስላ በቤይሩት የሚገኘው ማህበረሰብ ንብረት የሆነ ገንዘብ ወስዷል የተባለውን ጥርጣሬ እንዲመረመረው መንግስት በመጠየቁ የተደረገ ነው።›› አምባሳደር ውብሸት እንዳሉት፥ ኦዲት የተደረገው በአምባሳደር ነጋ ጸጋዬ በራሳቸው ነው።

 

King Felipe VI of Spain meet Ambassador of Ethiopia Nega Tsegaye... News  Photo - Getty Images

አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ ለስፔን ሃገር አምባሳደርነት ሲሾሙ ከስፔኑ ንጉስ ፌሊፔ ጋር የተነሱት ፎቶ (ምስል፤ ዋን አጓዶ/ጌቲ ምስሎች)

በሊባኖስ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገንዘቡ እንዲመለስላቸው የሚጠይቁ መልዕክቶች እንደረሷቸው አይክዱም።። ‹‹በርካታ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚያሰቅቅ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ እገነዘባለሁኝ። መረዳት የሚቻል ነው።››

በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያኔ በ2001 ዓም የጠፋውን ገንዘብ እንዲመለስላቸው ዘንድሮ በ2012 ቢጠይቁ አሳማኝ ይሆን እንደሆነ ሲጠየቁ የሰጡት መልስ አወንታዊ ነው።

‹‹በትክክል። ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር ስምምነት ያደረግነው ያኔ ድሮ ነው። ይህ ገንዘብ የመንግስት ንብረት አይደለም።፤ እንደዚህ ዓይነቱ ገንዘብ ሊመለስ የሚችልበት አሰራር ያለ ቢሆንም፥ በሊባኖስ ለሚገኙ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ንብረታቸው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። ዕውነታው ደግሞ እጃቸው ካሉበት ሰዎች በስተቀር የፌዴራሉ መንግስት ስለገንዘቡ መኖር የሚያውቀው ነገር የለም ስለነገሩ ማውራት እሰከጀመርንበት ጊዜ ድረስ።››

በአሁኑ ሰዓት የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም።፤ በአምባሳደር ውብሸት ድምሴ እንደተገለጸው፥ ዶር/ ቴድሮስ መጠኑ $640,000 ስለሆነው ነገር ጉዳይ እንዳወቁ በሊባኖስ መሠረቱን ላደረገው የኢትዮጵያውይን ማህበረሰብ እንዲመለስ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። (ምስል፡ ፋብሪስ ኮፈሪኒ/ኤ/ኤፍ/ፒ/ጌቲ ኢሜጅስ)

አንድ ዋና ቆንስል ንብረቶችን ከአንድ አገር ወደሌላ የሚልኩ እንደሆነ፣ በአዲስ አበባ ከሚገኝ አንድ ሰው ተሳታፊ እንደሚያስፈልገው አምባሳደር ውብሸት ይስማማሉ። ይህም አምባሳደር ነጋ የባንክ ማዛወሪያውን እንዲደረግ እና አምባሳደር ተክለአብ ከበደ በመጨረሻ ያከናወኑት ከመሆኑ ዕውነታ ጋረ የሚጣጣም ነው።

አምባሳደር ውብሸት በሰጡት ምስክርነት፥ ምናልባት ትክክል ከሆነ፥ የኢትዮጵያ ዋና ቆንስል የሆኑት አምባሳደር ሐሊማ መሐመድ፥ በቤሩት በነበራቸው የአገልግሎት ዘመን ቆይታ ሁሉ ዝምታን ከመምረጣቸው አስቀድሞ፥ ገንዘቡ ስለጠፋበት መንገድ በደንብ ምርመራ ያደረጉ መሆኑን ያስረዳል።

አምባሳደር ውብሸት ድምሴ፥ በንጽጽር በጉዳዩ ላይ ክፍት ሆነው መገኘታቸው የሚደብቁት እንደሌላ ወይም ጥቂት መሆኑን የሚያስመሰክር ነው። ዳሩ ግን፥ በጅዳ የቀድሞ ዋና ቆንስል የነበሩት እንደገለጹት፥ በጎደለው ገንዘብ ላይ መረጃ እንዲሰጥ ለእርሳቸው ጽህፈት ቤት ጥያቄዎች እንደደረሱ ያመኑ ቢሆንም፥ በይፋ ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተው አያውቁም። የእርሳቸውን ስምና ፊርማ የያዘ ሰነድ እንዳለ እና ስለዝርዝሮቹ እንደሚያውቁ እስከተነገራቸው ጊዜ ድረስ ለማንም ቢሆን እስከላይኛው የመንግስት የዕዝ ሰንሰለት ድረስ የገንዘቡ ጉዳይ ስለመድረሱ ምንም ምልክት አልሰጡም ነበር፤ ደግሞም ልክ በሊባኖስ እንዳሉት አቻዎቻቸው በጉዳዩ ላይ ከመነጋገር ተቆጥበዋል።

በተጨማሪም፥ አምባሳደር ውብሸት እንደሚናገሩት፥ ስለጉዳዩ መንግስት ያወቀው ከአመታት በኋላ እንደሆነ የሚጠረጥሩት የተሳሳተ ነው። ከዚህ በታች የሚገኘው ሰነድ የኢትዮጵያ መንግሰት ግምጃ ቤት ኃላፊዎች ስለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር ክፍያ ፓኬጅ በሚመለከት በሰኔ 10/2001 ቢዘገይ ያውቁ እንደነበረ ያሳያል። ይህም የሎቢ ድርጅቱ ክፍያውን ከተቀበለ አንድ ወር ቢሞላው ነው።

በ2006 እ.ኤ.አ. ሌላ ከጅዳ የኢትዮጳያ ቆንስላ የተገኘ ደብዳቤ ደግሞ አምባሳደር ውብሸት ደምሴን ሌላ ጎን ያወጣል።ሰነዱ 52 ገጽ የሚሆን በአምባሳደር ውብሸት በራሳቸው የተከተበ የውስጥ ማስታወሻ ሲሆን፥ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን የተጋለጠ እና እንዲጠብቋቸው በተመደቡባቸው ኢትዮጵያውያን የውጭ ባለሞያዎች ላይ ጫና ለመፍጠር ሲባል ኢምባሲዎች እና ቆንስላዎች ማድረግ ያለባቸውን የሚገልጽ መመሪያ ነው። ከእነዚህ ምክሮች መካከል፥ የገዢው ፓረቲ ፍልስፍና ሆነው በዓለም ዙሪያ ባሉ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዘንድ የሚያገለግሉ የማህበረሰብ ወኪሎችን ማመልመል ይገኛል።

የውብሸት ‹‹አጋርነት ግንባታ›› መመሪያ ትኩረቱን የሚያደርገው የተቃዋሚዎችን ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መጠራረግ እና የውጭ አገር ባለሙያዎችን ማህበረሰብ የመንግስትን ተረክ የሚቃረኑ ዜና ወይም ዘገባዎችን ስርጭት ለመታገል በሚደረገው ፍልሚያ የገዢው ታማኝ ካምፕ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በደምሳሳው፥ አምባሳደር ውብሸት ሲያደርጉ የተገኙት መንግስት ለዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከፍሎ ያሰራውን ሥራ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን እንዲያደርጉት መፈለጋቸው ነው።

በቤት ውስጥ ሥራዎች እንጀራ ፍለጋ ወደመካለኛው ምስረቅ የሚፈልሱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ይህንን የሚያደርጉት ሥራ አጥነትን፣ የከሰመ ዕድል እና ድህነትን ለማምለጥ ነው። እንደሊባኖስ ባሉ አገራት እስከገቡ ድረስ፥ የቤት ውስጥ ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው እጅ ይሽከረከራሉ ምክንያቱም በአሠሪዎቻቸው አስከፊ በደል እንዲደርስባቸው የሚያደርግ ከፋላ ስርዓት በመኖሩ ነው።  በሊባኖስ ህይወታቸውን የሚያጡ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ወኋላ ሲታሰብ እስከ 1995 እ.ኤ.አ. የቆየ እና በሊባኖስ ፍርድ ቤቶች ማንም ለፍርድ ቀርቦበት የማያውቀው ነው።

ሌላኛው ተጠቂዎች ቁጥራቸው የመብዛቱ ምክንያት የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ተቋማት በቤት ሠራተኞች ጥቃት እና ግድያ ገዳይ ጣልቃ አለመግባታቸው ነው። ገንዘብ ስለመጉደሉ በተመለከተም ለተነሳው ቅሬታ ምንም መልስ ያለመስጠታቸው ሊብራራ የሚችለው በዚህ ነው።

በሊባኖስ የሚገኙት ማህበረሰቦች ንብረት የሆነው መጠኑ $640,000 የአሜሪካ ዶላር የሆነ ገንዘብ ዱካው ከቤሩት ወደ ጅዳ እና በስተመጨረሻም በአሜሪካ የሚገኘው ዲ/ኤል/ኤ ፓይፐር መሆኑ በግልጽ የተረጋገጠ ነው። በኦፊሴላዊ ማህተም እና ፊርማዎች የተረጋገጡተ እና የተጠቀሱትን መረጃዎች የሚቃወም ምንም ነገር ቃለመጠይቅ ከተደረገላቸው ወገኖች ያቀረበ የለም። አምባሳደር ተክለአብ በድርቅና ክደዋል፤ የሚያስታውሱት ነገር እንደሌለ ቆይተው አሳባቸውን ከመለወጣቸው በፊት በመጀመሪያ እንደውም ከቤሩት ወደጅዳ በአስቸኳይ እንዲዛወር የተደረገ ገንዘብ የለም ብለውም ነበረ። አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ በበኩላቸው፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ዕውነቱ እንዳይመረመር የሚደረገውን የቤሩት ነዋሪ ጥረት አግደው እርሳቸው ተሳትፎ ያላቸው ስለመሆኑ በፋክስ በተረጋገጠው ማዛወሪያ ላይ ያለውን ስም አና ፊርማቸውን በሚመለከት ጋዜጠኞች ሊጠይቋቸው ሲሞክሩ ጆሯቸው ላይ ዘግተዋል።

ዛሬ ላይ በሊባኖስ የሚደርሰው የሰብዓዊነት ቀውስ

ዓመታት አልፈውም እንኳን፥ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቀድሞ ቆንስል አሳምነው ደበሌ ከገለጹት ቢብስ እንጂ የማያንስ ሰቆቃ ውስጥ አሁንም አሉ። በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ2019 እ.ኤ.አ. ያለው የገንዘብ መቀዛቀዝ በርካታ የአገሪቱን ሥራዎች ያደረገ በመሆኑ ከሥራ አጥነት፣ ኪሳቸው ባዶ በመሆን እና ለረሃብ ከመጋለጣቸው የተነሣ ከኅዳር ጀምረው ወደአገራቸው እንዲመለሱ ልመና እያቀረቡ ነበሩ። ከዚያ በማስከተል የኮቪድ -19 መከሰት ይህንን አባብሶታል። የታጎሉ፣ ሠራ አጥ፣ ረሃብ ሊገድላቸው የደረሱ ኢትዮጵያውያንን ወደአገር የመመለሱ ዕድል አነስተኛ ነው። በጉዳዩ ላይ ሲጠየቁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ገዱ አንዳርጋቸው በርካታ ተመላሾች ስለሚኖሩ ኳራንታይን ቦታዎችን ለማዘጋጀት ጊዜ ያስፈልገናል ብለዋል። ነገር ግን ለመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሻሜቦ ፊጣሞ እንደጠቀሱት በሊባኖስ የሚገኙ ዜጋ ሠራተኞች በመንግስት ቅድሚያ የሚሰጣቸው አይደሉም። በቅርቡ አምባሳደር ሻሜቦ በትዊተር ገጻቸው እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ ስለ110 ሚሊየን የሀብረተሰብ ጤና ለምን አያሳስባችሁም በበሽታው እንዳይጠቁ? ››

ለኢትዮጵያ መንግስት ሹማምንት በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደአገራቸው የመመለሱ ነገር እንዲሁ ያሰቡበት አለመሆኑን ግልጽ አድርገዋል። ዳሩ ግን እርዳታ፣ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ቢያንስ ርሃብ እና ማደሪያ ማጣት እንዳይጠናባቸው ፍራቻቸውን የሚያረግብ የሆነ ነገር በሊባኖስ ለሚንገላቱት ስደተኞች እጅግ ያስፈልጋቸዋል። የሆነ ሆኖ፥ አሁን እየተጉላሉ ያሉቱ፥ የዛሬ አስር ዓመት ሲታይ ያ የጠፋው $640,000 የአሜሪካ ዶላር ለአሜሪካ የሎቢ ድርጅት የተላለፈባቸውን ገንዘብ ያፈሩ ነበሩና።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s